Announcement በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ መምህራን እና ርዕሳነ መምህራን ዲጂታል መታወቂያ ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ።

በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ መምህራን እና ርዕሳነ መምህራን ዲጂታል መታወቂያ ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ።

28th March, 2026

በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ መምህራን እና ርዕሳነ መምህራን ዲጂታል መታወቂያ ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ።

(መጋቢት 17/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ መምህራን እና ርዕሳነ መምህራን ዲጂታል መታወቂያ ተደራሽ ለማድረግ ስምንት የመታወቂያ ማተሚያ ማሽን በመግዛት በህትመት ላይ መሆኑ ተገልጻል። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ ዲጅታል መታወቂያው ከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ሴክተሩን ዲጅታላይዝ ለማድረግ እያከናወነ የሚገኘውን ስራ ውጤታማ ለማድረግ የመምህራንን እና የርዕሳነ መምህራንን መረጃ ወደ ኢ ስኩል ሲስተም በማስገባት ዲጅታል መታወቂያ የማዘጋጀት ስራ መጀመሩን ጠቁመው ዲጅታል መታወቂያው ስካን የሚደረግ በመሆኑ  ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት መድቦ መምህራን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ካደረገው የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ጋር በተገናኘ በአንዳንድ ህገወጥ አካላት የተዘጋጁ ፎርጅድ መታወቂያዎች አገልግሎት ላይ እንዳይውሉ የሚያደርግ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም ዲጅታል መታወቂያው መምህራኑ ወጥ የሆነ መታወቂያ ኖሯቸው የተለያዩ አገልግሎቶችን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ከማድረጉ ባሻገር መረጃቸውን በሲስተሙ አማካይነት በፍጥነት ማግኘት እንዲችሉ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በተያያዘ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ለክፍለ ከተማ የዘርፉ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በኢ ስኩል ሲስተም አተገባበርና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ሲስተሙን ባለማው ትሪያ ትሬዲንግ አማካይነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

.

Copyright © All rights reserved.