የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ትራንስፎርም በማድረግ ሞዴል ተቋማት ለማብዛት በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡
(ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘርፈብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ትምህርት ቤቶችን ትራንስፎርም ለማድረግና ሞዴል የትምህር ተቋማትን ለማበራከት ቢሮው እያከናወነ ያለውን ሥራ ውጤታማ ለማድረግ በትምህርት ቤቶች ያለውን አፈፃፀም በመመልከት ለተሻለ ስኬት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጻል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ጥላዬ ዘውዴ ከተማ አስተዳደሩ ህጻናት ላይ መስራት ሀገር ላይ መስራት ነው ብሎ ለህጻናት ምቹ የመማሪያ አካባቢ ለመፍጠር ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑን በመግለጽ በ247 የመንግስት ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዜጎችን ልመቅረፅ ልዩ ትኩረት በመስጠት በግብአትና የማስተማሪያ ስነዘዴ እየቀረጸ ሲያስተገብር መቆየቱን ገልጸዋል፡፡
አቶ ጥላዬ አያይዘውም ህጻናት የሚማሩበት አካባቢ በውስጣዊና ውጫዊ ገጽታው ሳቢ እንዲሁም የማስተማሪያ ዘዴው በጨዋታ እንዲሆን ቢሮው ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ለሚያስፈልገው አካል ስልጠና በመስጠት ድጋፍና ክትትል እያደረገ መቆየቱን ገልጸው በ2019 የትምህርት ዘመንም ከዚህ የጎለበተ ስራ ለማከናወን እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ዘርፈብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ በላይነሽ የሻው ትምህርት ቤቶችን ትራንስፎርም በማድረግ ሞዴል ተቋማት ለማብዛት የሚያስፈልጉ የግብአት ድጋፍ ለማድረግ መረጃዎችን መለየት አስፈላጊ በመሆኑ አዳዲሶቹን ጨምሮ በ 247 ተቋማት ላይ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ ለዚህ መሳካት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡
.