Announcement ቢሮው ለ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ደንብ ልብስን ጨምሮ የተለያዩ ግብአቶች ስርጭት በማካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ቢሮው ለ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ደንብ ልብስን ጨምሮ የተለያዩ ግብአቶች ስርጭት በማካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

29th August, 2026

(ነሀሴ 22/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ተማሪዎች በአዲሱ የትምህርት አመት የሚጠቀሙባቸውን የደንብ ልብሶች የመማሪያ መጽሀፎች እና ደብተሮችን በማሰራጨት ላይ መሆኑን የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡

ግብአቶቹን ተማሪዎች ለ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት ምዝገባ በሚያካሂዱበት ወቅት እንዲወስዱ በመደረግ ላይ መሆኑን የቢሮው የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ምስራቅ ብርሀነ መስቀል አስታውቀዋል፡፡

ዳይሬክተሩዋ አያይዘውም ከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ግብአቶቹን ማቅረብ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር መሻሻል ላይ ከፍተኛ እድገት በመመዝገብ ላይ መሆኑን ገልጸው የግብአት አቅርቦቱ ከፍተኛ በጀት  ወጪ ተደርጎበት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ያለምንም ጫና ተከታትለው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል እንደመቅረቡ ትምህርት ቤቶች ግብአቶቹን በአግባቡ በማሰራጨት የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል መስራት  እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.