Resource የትምህርት ተቋማትን የ2017 ዓ.ም የግማሽ አመት አፈጻጸም መሰረት አድርጎ የተካሄደው ምዘና ተጠናቀቀ።

የትምህርት ተቋማትን የ2017 ዓ.ም የግማሽ አመት አፈጻጸም መሰረት አድርጎ የተካሄደው ምዘና ተጠናቀቀ።

22nd February, 2025

የትምህርት ተቋማትን የ2017 ዓ.ም የግማሽ አመት አፈጻጸም መሰረት አድርጎ የተካሄደው ምዘና ተጠናቀቀ።

(የካቲት 12/2017 ዓ.ም) ምዘናው ከቢሮ ጀምሮ በክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እንዲሁም በሁሉም የመንግስት አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች  የቁልፍ ውጤት አመላካች ተግባራት እና የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ እቅድ አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ ነው የተካሄደው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ   የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ፈንታሁ እያዩ  ዛሬ የየነበረውን የምዘና ሂደት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው አዲስ ምዕራፍ 1ኛ ደረጃ፣ልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ፍሬህይወት ቁ.1 አንደኛ ደረጃ እንዲሁም ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቆጣሪ አንደኛ ደረጃ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአቃቂ ብሩህ ተስፋ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና  ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ጎሮ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በምዘናው ለሚሳተፉ 540 ለሚሆኑ መዛኞች በምዘናው መስፈርትና አካሄድ ዙሪያ ኦረንቴሽን ከመስጠት ጀምሮ በተከናወኑ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ምዘናው በሁሉም የትምህርት ተቋማት ያለምንም ችግር መካሄዱን በምልከታ መረጋገጡን የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ፈንታሁን እያዩ ጠቁመው በቀጣይ በምዘናው ግብረ መልስ መሰረት አፈጻጸማቸው ከፍተኛ ለሆኑ ተቋማት እውቅና በመስጠት እና ዝቅተኛ የሆኑትን በመደገፍ ወደተቀራራቢ ደረጃ እንዲመጡ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ አመላክተዋል።


.

Copyright © All rights reserved.