About 10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በወዳጅነት አደባባይ በድምቀት ተከፈተ።

10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በወዳጅነት አደባባይ በድምቀት ተከፈተ።

26th April, 2025

10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በወዳጅነት አደባባይ በድምቀት ተከፈተ።

(ሚያዝያ 16/2017) ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት "በፈጠራ ስራ የተካነ ትጉህ ትውልድ ለሀገር ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው አውደ ርዕይ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ ተማሪዎችና መምህራን የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ለህብረተሰቡ ለዕይታ ቀርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና የመርሀ ግብሩ የክብር እንግዳ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለይም በከተማችን አዲስ አበባ  የተለያዩ ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመው ይህ የፈጠራ ስራ ከፍ ወዳለ ደረጃ እንዲሸጋገር በተማሪዎችና መምህራን የሚሰሩ የፈጠራ ስራዎችን በዚህ መልኩ አውደ ርዕይ በማዘጋጀት ማበረታታት እንደሚገባ በመግለጽ  ከተማ አስተዳደሩም በተማሪዎችና መምህራን የሚሰሩ የፈጠራ ስራዎች ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በትምህርት ሴክተሩ የሚዘጋጅ የሳይንስ የፈጠራ አውደ ርዕይ  በተማሪዎችና መምህራን የሚሰሩ የፈጠራ ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ ለህብረተሰቡ ከማስተዋወቁ ባሻገር የፈጠራ ባለቤቶቹን ለተሻለ ስራ የሚያነሳሳ ተግባር መሆኑን ገልጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ ለትምህርት ዘርፉ ለሚያደርጉት የቅርብ ድጋፍና ክትትል ምስጋና አቅርበዋል።

ዶክተር ዘላለም አያይዘውም ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ከተማ ድረስ አውደ ርዕዩ በስኬት እንዲካሄድ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበው   የከተማው ነዋሪዎችም ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ለዕይታ ክፍት በሆነው አውደ ርዕይ በመገኘት የፈጠራ ባለቤት የሆኑ ተማሪዎችን እና መምህራንን እንዲያበረታቱ ጥሪ አስተላልፈዋል።

.

Copyright © All rights reserved.