(ሚያዝያ 4/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር የመዝጊያ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ስቴድየም በመከናወን ላይ ይገኛል።
የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ዉድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ ንቁና ብቁ ትዉልድን እንፈጥራለን! በሚል መሪ ቃል በ11ክፍለ ከተሞች በ10 የስፖርት አይነት ሲካሄድ የቆየዉ ከተማ አቀፍ የመምህራንና የተማሪዎች የስፖርት ሊግ ዉድድር የመዝጊያ መርሀ ግብር ላይ የፌደራል እና ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ተማሪዎች ፣ መምህራን እና የስፖርት ቤተሰቦች ታድመዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የወንዶች መምህራን የእግር ካስ የፍጻሜ ጨዋታ በየካ ክፍለ ከተማና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የተጀመረ ሲሆን ንፈስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ዉጤት እየመራ ይገኛል፡፡
በቀጣይም በጉለሌ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማዎች የሴቶች መምህራን የገመድ ጉተታ የፍጻሜ ውድድር እና የአመራሮች የእግር ካስ ውድድር የሚከናወን ይሆናል፡፡
.