(ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍ እና የእቅድ ዝግጅትና ድጋፍ ዳይሬክቶሬቶች የ3ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ላይ ድጋፍና ክትትል ለወረዳ ት/ጽ/ቤቶች ለሚያደርጉ ባለሞያዎች ኦረንቴሽን ሰጥተዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በኦረንቴሽኑ ላይ ተገኝተው እንዳሉት ቢሮው በተለያየ ጊዜ የተግባራትን አፈፃፀም ለማሻሻል ድጋፍና ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመው የድጋፍና ክትትል ሂደቱ ስራው ያለበትን ቁመና የሚያሳይ እንደሆነ ተናግረዋል::
የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ ኦረንቴሽኑን በሰጡበት ወቅት እንዳሉት የክትትልና ድጋፍ ስራው ተቋማት እየሰጡ ያለው አገልግሎትና በእቅድ የተያዙ ተግባራት አፈፃፀም በማወቅ ለቀጣይ ቀሪ ወራት መፍትሄ ለማበጀት እንዲሁም የተሻለ አፈፃፀም ካላቸው ጋርም ተሞክሮ ለማስፋትና ልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንዲቻልና ግብዓት የሚሆኑ አጋዥ ነጥቦች የሚገኝበት እንደሚሆን አብራርተዋል::
አያይዘውም ድጋፍና ክትትሉ በወረዳ ደረጃ ሚያዚያ 29 እና 30/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡
.