Announcement በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ የትምህርት መሰረተ ልማቶች የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ ባሻገር

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ የትምህርት መሰረተ ልማቶች የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ ባሻገር

25th November, 2026

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ የትምህርት መሰረተ ልማቶች የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ ባሻገር በክፍለከተማው የፈረቃ ትምህርት እንዲቀንስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተገለጸ።


(ህዳር 14/2019 ዓ.ም) በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ የትምህርት መሰረተ ልማቶች የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ ባሻገር በክፍለከተማው የፈረቃ ትምህርት እንዲቀንስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ግንባታቸዉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት በጀመሩ ተቋማት እንዲሁም የማስፋፊያ ግንባታ እየተካሄደ በሚገኝባቸው እና በቀጣይ አዳዲስ ግንባታዎች በሚጀመርባቸው ተቋማት ላይ ያለው መረጃ እንደሚያሳይ ተመላክቷል።
 

ግንባታቸው ተጠናቆ ዘንድሮ ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ የመማር ማስተማር ስራ በጀመረው ድሬ ጎራ ትምህርት ቤት እና በቤተል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም የባለ አራት ወለል ህንጻ ግንባታ እየተካሄደ በሚገኝበት ጀጄነራል ዋቆ ጉቱ ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት በቅርቡ አዳዲስ የማስፋፊያ ግንባታዎች በሚጀመሩባቸው ቡርቃ ቡሩሩ፣ጀሞ እና ረጲ ጃፓን ትምህርት ቤቶች ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ለትምህርት ልማት ስራዉ ስኬታማነት ትልቅ ሚና እንደላቸው ተመላክቷል።
 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በክፍለ ከተማው በከፍተኛ በጀት ደረጃቸውን ጠብቀው ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመሩትም ሆኑ በቀጣይ የሚገነቡ አዳዲስ የትምህርት መሰረተ ልማቶች የትምህርት ጥራትን እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው በከፍተኛ በጀት ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመሩትን ተቋማት በአግባቡ በመጠቀም የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባርን ማላቅ እንደሚገባ በመግለጽ በቀጣይ የተጀመሩ የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በማጠናቀቅ እንዲሁም አዳዲስ ግንባታዎችን በፍጥነት በማስጀመር ለመማር ማስተማር ስራው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል አስፈላጊውን ስራ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።



የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ሰራ አስፈጻሚ ሙሉነህ ደሳለኝ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ የትምህርት መሰረተ ልማቶች የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ከማረጋገጥ ባሻገር የፈረቃ ትምህርት እንዲቀንስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸው ክፍለ ከተማው የተጀመሩትንም ሆነ አዳዲስ የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለመማር ማስተማር ስራው እንዲውሉ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

.

Copyright © All rights reserved.