(ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍ እና የእቅድ ዝግጅትና ድጋፍ ዳይሬክቶሬቶች የ3ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ድጋፍና ክትትል ማድረጋቸዉን አሳውቀዋል፡፡
ድጋፍና ክትትሉ በመደበኛ እንዲሁም በሪፎርም ስራዎች ስኬታማ የስራ አፈጻጸም መኖሩን የስራ ክፍሉ የሚያረጋግጥበት አንዱ መንገድ መሆኑን የገለጹት የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ በየስራ ክፍሉ ያሉ ስራዎች ወጥ የሆነ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ብሎም ተገቢ የአገልግሎት አሰጣጥ መኖሩን በማየት ክፍተት ያለበትን የስራ ክፍል ለመደገፍ እንደሚያስችል አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም ቢሮው የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ትኩረት በማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውሰው፤ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የትኩረት መስኮችና ዝርዝር ተግባራት ያካተተ ቼክሊስት በማዘጋጀት ስራው የተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
.