ማስታወቂያ
ቀን- 12/05/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በስሩ ለሚገኙ ከ1ኛ ደረጃ እስከ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የመምህራን ቅጥር ማስታወቂያ በቀን 21/12/2016 ዓ.ም ማዉጣቱ ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሰረት ከቀን 13-14/3/2017 ዓ.ም የዶክመንት ማጣራት ስራም ተሰርቷል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ለ1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በአይሲቲ፣ ሂሳብ፣ አፋን ኦሮሞ፤ ገዳና እርሻ የትምህርት ዓይነቶች ዶክመንታችሁን የማጣራት ስራ አስደርጋችሁ በመጠባበቅ ላይ ካላቹሁት ውስጥ ስማችሁ በት/ቢሮ ድህረ-ገፅ አማራጮች ላይ የተገለፀው ተወዳዳሪዎች ብቻ -
ወደ
1. በዜሮ ዓመት/በጀማሪ መምህርነት እና በአገልግሎት ተወዳድራችሁ ያለፋችሁ የክፍለ ከተማ ምደባችሁን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ቴሌግራም እና ፌስ ቡክ ገፅ አማራጮች ላይ በማየት በዜሮ ዓመት/በጀማሪ መምህርነት/ የተመደባችሁ ተመደባችሁበት ክፍለ ከተማ ከጥር 13- 16:017 ዓም ድረስ ብቻ በአካል በመሄድ ሪፖርት እንድታደርጉና ቅጥር እንድትፈፅም ::
2 በአገልግሎት ቅጥር የምትፈፅሙ ከቅድመ አንደኛ እስከ 12ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በማስተማር ብቻ የሰራችሁበትን አገልግሎት የምታመጡ በአገልግሎት ያመለከታችሁ መምህራን መልቀቂያ ስትሰሩበት ከነበረው ክልል የምታመጡ ጥር 16/2017 ዓ.ም ትምህርት ቢሮ 4ኛ ፎቅ የመትት/ኤ/ል/ዳይሬክቶሬት በመምጣት የክልል ደብዳቤ እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ--
✓ ከተለያዩ የመንግስት ት/ቤቶች በአገልግሎት የምትመጡ በትምህርት ቢሮው የደረጃ እድገት መሰላልና በቅጥር ማስታወቂያው መሰረት እስከ መምህርነት ደረጃ እድገት የደረሱ ተወዳዳሪዎች ብቻ የምናስተናግድ መሆኑን እያሳወቅን ከዚህ ውጪ ከዚህ በላይ/ በሆነ አገልግሎት ይዞ ለመምጣት በሚሞከረው እንግልት ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ የማንሆን መሆናችንን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡ ✓ ሁሉም አመልካች ሲመጣ ኦርጂናል ዶክመንትና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ መገኘት
ይኖርበታል፡፡
ማብራሪያና ቅሬታ ያለው አመልካች በ17/5/2017ዓ.ም. ብቻ በአካል
ይኖርበታል፡፡
✓ ከተጠቀሰዉ ቀናት ውጭ ለሚመጣ አመልካች የማናስተናግድ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።