Resource የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

21st January, 2025

የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

(ጥር 12/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ ማኔጅመንት አባላትና የትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። 

በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሀንስ ተስፋዬ   ከማይክሮ ፋይናንስና ቁጠባ ባህል ጋር የተገናኘ ሰነድ በማቅረብ እውቀታቸውን ያካፈሉ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ  የቁጠባ ባህልን በማዳበር ለመለወጥ መስራት ጥቅሙ ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ሰራተኞች በቢሮ ባለው የቁጠባ ማህበር አባል በመሆን በችግራቸው ጊዜ ከቆጠቡት በመውሰድ  መፍትሄ መስጠት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

, , .

Subscribe to receive inspiration, ideas, and news in your inbox.

Copyright © All rights reserved.