የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ልዩ ትኩረት በመስጠት የልዩ ፍላጎት ድጋፍ መስጫ ማዕከላት እንዲጠናከሩና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸው ተገቢ የመማር ማስተማር አገልግሎት በማግኝት የትምህርት ውጤታማነት እንዲጎለብት እያከናወናቸዉ የሚገኙ ስራዎችን በማጠናከር በዛሬው እለትም ለተመረጡ የልዩ ፍላጎት ድጋፍ መስጫ ማዕከላት የእገዛ መሣሪያዎች (Assistive devices) ድጋፍ አድርጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በልዩ ፍላጎት ድጋፍ መስጫ ማዕከላት የእገዛ መሣሪያዎች (Assistive devices) ግብዓቶች ስርጭት መርሀ ግብር ላይ ተገኝተው ለተመረጡ የድጋፍ መስጫ ማዕከላት ከቢሮ እስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ጋር በመሆን ግብዓቶችን አስረክበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን የተለያዩ ስራዎችን በማናወን ላይ መሆኑን የገለጹት ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የመስማት ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የተለያዩ ግብዓቶችን ማለትም Audiometer sentidestop fleyair and Bone standalone, Head phone, Otoscopes, Hearing aids እና ሌሎችን በማሰራጨትና በተቋቋሙ የእገዛ መሣሪያ ክፍሎች (Assistive Device Room) ላይ እንዲደራጁና ተማሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን፤ ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች ኬን ፣ ስለትስታይለስና የተለያዩ ግብዓቶች ፣ የአካል እንቅስቃሴ ችግር ላለባቸው ዊልቸር ፣ ክራንች ፣ ዎከር እንዲቀርብ በማድረግ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንደማንኛውም መደበኛ ተማሪዎች ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸው ተገቢ የመማር ማስተማር አገልግሎት ማግኝት እንዲችሉ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ሀላፊው አክለዉም ዛሬ ለተመረጡ የልዩ ፍላጎት ድጋፍ መስጫ ማዕከላት የተሰራጩ የእገዛ መሣሪያዎች (Assistive devices) መምህራን ለተማሪዎች በሚመች የማስተማር ስነ ዜደ በመጠቀም እንዲያስተምሩ እና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ በተሻለ መልኩ እንዲደግፉና እንዲያግዙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡
ድጋፉ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በጉዳት ዓይነትና ደረጃቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፣ ተማሪዎች የመስማት ችሎታ ምርመራዎችን እንዴት ማከናወን እንደሚቻል እንዲያውቁ ፣ የተለያዩ የመስማት ችግር ያለባቸው ተማሪዎች የኦዲዮግራም(db) ትርጓሜን እንዲያገኙና እንዲረዱ ፣ ኦዲዮሜትሪ ሴንቲዮሮ ዴስክቶፕ በመጠቀም የመስማት ደረጃን ለመለካት ፣ ተማሪዎች ፣ የትምርት ቤቱ ማህበረሰብ እና በሳተላይት የምገኙ ት/ቤቶችንና ማህበረሰቡን ለማገዝና የልዩ ፍላጎት ድጋፍ መስጫ ማዕከላትን ለማጠናከር እንደሚረዳ ተጠቁሟል፡፡