በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
(የካትት 28/2017 ዓ.ም) በምልከታው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ባሻገር የቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሌሊስቱ ተስፋዬና የክፍለ ከተማው የኮንስትራክሽንና ዲዛይን ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋዬ አያና ተሳታፊ ሆነዋል።
በምልከታው ጋራ ጉሪ ፣ አቢ ጃርሶ ፣ ቤኬ እና ድድቢሳ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የታዩ ሲሆን በተቋማቱ ግንባታቸው እየተከናወነ እና እየተጠናቀቁ የሚገኘው ህንጻዎች የታዩ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠው ጊዜ ጥራታቸው ተጠብቆ በፍጥነት በመገንባት ላይ መሆናቸውን በምልከታ ማረጋገጣቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው የክፍለ ከተማ አስተዳደርም ለፕሮጀክቶቹ በጥራት መገንባት ለነበረው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ የቀሩ ስራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
.