Resource ከተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም አተገባበር ጋር በተገናኘ በጎሮ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልምድ ልውውጥ መርሀግብር ተካሄደ።

ከተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም አተገባበር ጋር በተገናኘ በጎሮ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልምድ ልውውጥ መርሀግብር ተካሄደ።

11th January, 2025

ከተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም አተገባበር ጋር በተገናኘ በጎሮ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልምድ ልውውጥ መርሀግብር ተካሄደ።

(ጥር 2/2017 ዓ.ም) በልምድ ልውውጡ የክፍለ ከተማ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ቡድን መሪዎችና የጎልማሶች ትምህርት ባለሙያዎች ፣ የተፋጠነ ትምህርት ተግባራዊ ከሚደረግባቸው ትምህርት ቤት የመጡ ርዕሳነ መምህራን እና አመቻቾች እንዲሁም  ጉዳዩ የሚመለከታቸው የቢሮ ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት ጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም በተለያዩ ምክንያቶች መደበኛውን ትምህርት መማር ላልቻሉ እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ለሆኑ ህጻናት የሚሰጥ ፕሮግራም መሆኑን ጠቁመው በከተማ አስተዳደሩ ከ2014ዓ.ም ጀምሮ ፕሮግራሙ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ በመግለጽ በዛሬው ልምድ ልውውጥ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በተቋሙ ያዩትን ተሞክሮ መሰረት በማድረግ በየትምህርትቤታቸው ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም በከተማ አስተዳደሩ በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች በሳምንት ለ5ቀናት በቀን ለ7 ሰአታት እየተሰጠ እንደሚገኝ የቢሮው የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ባለሙያው አቶ ጌታቸው በላይነህ ገልጸው ተማሪዎቹ ለ10ር ወር ትምህርታቸውን ተከታትለው በማጠናቀቅ በመደበኛው ትምህርት 4ኛ ክፍል ገብተው ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ አስታውቀዋል።

የልምድ ልውውጡ ተሳታፊዎች በትምህርት ቤቱ በመዘዋወር የተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም አተገባበሩን የተመለከቱ ሲሆን ተቋሙ ፕሮግራሙ ውጤታማ እንዲሆን በማከናወን ላይ የሚገኘው ተግባር ልምድ የሚቀሰምበት በመሆኑ ቢሮው የልምድ ልውውጥ መርሀግብሩን ማዘጋጀቱ ተገቢ መሆኑን አመላክተዋል

.

Copyright © All rights reserved.