Resource ቢሮው ያወረደው የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት አስታወቀ።

ቢሮው ያወረደው የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት አስታወቀ።

21st December, 2024

ቢሮው ያወረደው የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት አስታወቀ።

(ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም) አዳሪ ምህርት ቤቱ ዘወትር ሐሙስ ማለዳ በሰልፍ ስነስርአት ላይ በሒሳብ ክበብ አባላት አማካይነት ተማሪዎች ከሒሳብ ትምህርት ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ የሚያቀርበው መርሀ ግብር በዛሬው እለትም ቀጥሎ ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግ ያዘጋጀው ስትራቴጂ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ትምህርት ቤቱ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን የእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት ሀና ፀጋዬ ገልጸው ተማሪዎችን በሒሳብ ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ የሒሳብ ክበቡን ከመደገፍ ጀምሮ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

የአዳሪ ትምህርት ቤቱ የሒሳብ መምህር እና የክበቡ ተጠሪ መምህር ዲንሳ ረጋሳ በበኩላቸው በትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በሒሳብ ትምህርት ውጤታማ እንዲሆኑ ዘወትር ሀሙስ ማለዳ በሰልፍ ስነስርአት ላይ በክበቡ አባላት አማካይነት የተለያዩ መልዕክቶች እንደሚተላለፉ ጠቁመው መምህራንም በክፍል ውስጥ ተማሪዎቹ በሒሳብ ትምህርት ውጤታማ የሚሆኑበትን የማስተማሪያ ስነዘዴ ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆናቸውን አመላክተዋል።

የተማሪዎችን የሒሳብ ትምህርት ውጤት በመተንተን ያሉበትን ደረጃ በመለየት የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎች እንደሚደረጉ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ሱፐርቫይዘር አቶ ፀጋዬ አሰፋ ገልጸዋል።

, , .

Subscribe to receive inspiration, ideas, and news in your inbox.

Copyright © All rights reserved.