Resource ትምህርት ቢሮ ያወረደውን የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ ተግባራዊ በማድረጉ የተማሪዎች ውጤት መሻሻል ማሳየቱን የአቃቂ ብሩህ ተስፋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስታወቀ።

ትምህርት ቢሮ ያወረደውን የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ ተግባራዊ በማድረጉ የተማሪዎች ውጤት መሻሻል ማሳየቱን የአቃቂ ብሩህ ተስፋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስታወቀ።

03rd January, 2025

ትምህርት ቢሮ ያወረደውን የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ ተግባራዊ በማድረጉ የተማሪዎች ውጤት መሻሻል ማሳየቱን የአቃቂ ብሩህ ተስፋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስታወቀ።

(ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም) ትምህርት ቤቱ በስትራቴጂው መሰረት የተማሪዎችን የመጻፍ፣የማንበብ እና የማስላት ብቃትን መሰረት በማድረግ ለይቶ በተከታታይ ባደረጋቸው ድጋፎች ተማሪዎቹ በሁለቱ የትምህርት አይነቶች ውጤታቸው በመሻሻል ላይ መሆኑን በምዘና ማረጋገጡን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ታደሰ አለሙ ገልጸው ተቋሙ ውጤታማ መሆን የቻለው ከወላጆች፣መምህራን እና ተማሪዎች ጋር የአራትዮሽ ፊርማ ተፈራርሞ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ በመቻሉ እንደሆነ አስረድተዋል።

ርዕሰ መምህሩ አያይዘውም ትምህርት ቤቱ በ2016 በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ያስፈተናቸው ተማሪዎች በሙሉ ወደ 9ኛ ክፍል መዘዋወራቸውን ጠቁመው ቀደም ሲል በነበሩበት ፉሪ አንደኛ ትምህርት ቤት የነበራቸው ውጤታማነት በዚህኛው ትምህርት ቤት መደገሙን በመግለጽ በዚህ አመትም የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉንም አስገንዝበዋል።

ትምህርት ቤቱ ለሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት በሰጠው ትኩረት ለተለያዩ ትምህርት ተቋማት ሞዴል መሆን የቻሉ ማዕከላት ማቋቋሙን የማዕከላቱ ተጠሪ መምህራን ጠቁመው ተማሪዎቹ ከማዕከላቱ ባሻገር ትምህርት ቤቱ ባቋቋመው የኦዲዮ ቪዥዋል ክፍል  በድምጽና ምስል የተደገፈ ትምህርት በማግኘት ላይ በመሆናቸው ውጤታቸው በመሻሻል ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቱ ስርአተ ትምህርቱን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረጉ የተማሪዎቹን የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት በማሻሻል ላይ እንደሚገኝ በተለያየ ጊዜ በተደረገ ድጋፍና ክትትል መረጋገጡን የትምህርት ቢሮ የስነዜጋ መሻሻልና የተማሪዎች ጉዳይ ባለሙያ አቶ ባይሳ ፀጋዬ ገልጸው ከመደበኛው የመማር ማስተማር ስራው ባሻገር ተቋሙ በከተማ ግብርና ስራም ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን አመላክተዋል።

, , .

Subscribe to receive inspiration, ideas, and news in your inbox.

Copyright © All rights reserved.