የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክቶሬት በe-school ሲስተም ላይ የሲስተሙ አልሚ ድርጅት ማስተካከያ በማድረግ ያቀረበ መሆኑን በመጥቀስ ማስተካከያ በተደረገባቸው ጉዳዮች ላይ ማረጋገጫ እየተሰጠ መሆኑን አሳውቋል፡፡
በማረጋገጥ ሂደቱ ላይ ሶፍትዌሩን ያለማው ድርጅት፤ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና ትምህርት ቢሮ በጋራ በመሆን ድርጅቱ ያደረጋቸው ማስተካከያዎች ላይ ግምገማ ተደርጋል፡፡
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ በe-school ሲስተም ላይ መጠነኛ ማስተካከያ የሚፈልጉ ጉዳዮች በተለያየ ጊዜ ይነሱ እንደነበር ጠቁመው የሶፍትዌር አልሚ ድርጅቱ የተነሱ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ ገለጻ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም በሲስተሙ ላይ የተደረጉ ማስተካከያዎችን በአግባቡ በመረዳት መረጃን በቀላሉ ለማግኘትና የውስጥ ስራን ቀልጣፋ ለማድረግና በወጥነት ስራን በርብርብ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በሶፍትዌሩ ላይ የተደረጉ ማስተካከያዎች ሲቀርቡ የሁሉም ክፍለ ከተማ አይሲቲ ባለሙያዎችና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎችና ተገኝተዋል፡፡
.