Resource የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከፍተኛ ወጪ የገዛቸውን የተለያዩ ቁሳቁሶች ለቪዥን የአይነስውራን አጸደ ህጻናት ትምህርት ቤት አበረከተ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከፍተኛ ወጪ የገዛቸውን የተለያዩ ቁሳቁሶች ለቪዥን የአይነስውራን አጸደ ህጻናት ትምህርት ቤት አበረከተ።

01st March, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከፍተኛ ወጪ የገዛቸውን የተለያዩ ቁሳቁሶች ለቪዥን የአይነስውራን አጸደ ህጻናት ትምህርት ቤት አበረከተ።

(የካቲት 21/2017 ዓ.ም) ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ የድምጽ ኳሶች፣የብሬል መዝገበ ቃላት ፣ኬን የድምጽ ሰአቶች፣የብሬል ካርታዎች፣ሼልፍ፣የድምጽ ካልኩሌተሮች፣የብሬል ወረቀቶች፣ስሌት ስታይለስ፣አባከስ፣ሄድ ፎን፣የቆሻሻ ቅርጫቶች፣የማጉያ ሌንስ፣ሳይንስ ኪት፣የቋንቋ ኪት እና ስኔይል ቻርት በቢሮው አማካይነት ድጋፍ ተደርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ቪዥን የአይነስውራን አጸደ ህጻናት ትምህርት ቤት ወላጆች ልጆቻቸውን ከተለያዩ አከባቢዎች የተለያዩ ጫናዎችን በመቋቋም እያመጡ የሚያስተምሩበት ተቋም እንደመሆኑ ቢሮው ህጻናቱ በትምህርታቸው ውጤታማ ሆነው የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ እንዲሆኑ በማሰብ የቁሳቁሶቹን ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመው ትምህርት ቢሮ ለትምህርት ቤቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስገንዝበዋል።

የንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራአስፈጻሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ በበኩላቸው ቪዥን የአይነስውራን አጸደ ህጻናት ትምህርት ቤት የሚማሩ ህጻናትን የመንከባከብም ሆነ የመደገፍ ተግባር የሁሉም የህብረተሰብ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸው የክፍለ ከተማው አስተዳደርም ለትምህርት ቤቱ አቅም በፈቀደ ሁሉ ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለቪዥን የአይነስውራን አጸደ ህጻናት ትምህርት ቤት የግብአት ድጋፍ  ሲያደርግ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ጠቁመው ትምህርት ቤቱም ቁሳቁሶቹን ለተማሪዎቹ በአግባቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንደሚገባው አስታውቀዋል።

.

Copyright © All rights reserved.