የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት በመምህራን እና በትምህርት ባለሙያዎች የተሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ጽብረቃ አካሄደ።
(ጥር 23/2017 ዓ.ም) የጽብረቃ መድረኩ "በጥናትና ምርምር የበለጸገ ትምህርት ለላቀ የተማሪዎች ውጤት" በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን በመርሀግብሩ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ እንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ ሱፐርቫይዘሮችና የወረዳ ትምህርት ጽህፈት የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዮሀንስ ተስፋዬ(ዶክተር) በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት በመማር ማ ስማር ሂደቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በማሰብ በመምህራን እና በትምህርት ባለሙያዎች የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ጽብረቃ የሚደረግበትን መድረክ በማዘጋጀት ስራዎቹ እውቅና እንዲያገኙ ማድረጉ የሚያስመሰግነው ተግባር መሆኑን ጠቀመው ቢሮው በትምህርት ቤትም ሆነ በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ለሚፈለገው አላማ እንዲውሉ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የስራ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ አቤቤ በበኩላቸው በመርሀ ግብሩ በ2017ዓ.ም በስድስት ወራት ውስጥ በትምህርት ቤትና በክፍለ ከተማ ደረጃ የተሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች መቅረባቸውን ገልጸው የጥናትና ምርምር ስራዎቹ በትምህርት ሴክተሩ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ እንዲቻል አቅጣጫ ጠቋሚ የሆኑ የመፍትሄ ሀሳቦች የሚቀርቡባቸው በመሆኑ ጽህፈት ቤቱ ለዘርፉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስገንዝበዋል::
በጽብረቃ መርሀግብሩ በመምህራን እና በትምህርት ባለሙያዎች የተሰሩ ስምንት የጥናትና ምርምር ስራዎች መቅረባቸውን የጽህፈት ቤቱ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ቡድን መሪ አቶ ተሾመ ዘውዴ ጠቅሰው ከቀረቡት ስራዎች ውስጥ በዳኞች በሚሰጥ ነጥብ የተሻለ ሆኖ የሚመረጠው አንድ የጥናትና ምርምር ስራ ወደ ትምህርት ቢሮ እንደሚላክ አስታውቀዋል።