Resource የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቱሪስት መስህብ የሆነችውን የሉሲ ምስል ስጦታ አበረከተ፡፡

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቱሪስት መስህብ የሆነችውን የሉሲ ምስል ስጦታ አበረከተ፡፡

15th February, 2025

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቱሪስት መስህብ የሆነችውን የሉሲ ምስል ስጦታ አበረከተ፡፡

(የካቲት 7/2017 ዓ.ም) ስጦታው በክልሉ በሚገኘው አፋር ታለንት አካዳሚ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሉት ሶስት አዳሪ ትምህርትቤቶች በነበራቸው ጉብኝት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከአቀባበል ጀምሮ ላደረገላቸው ድጋፍ መበርከቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የፈተና ክፍል ኃላፊ አቶ መሀመድ ሰኢድ  አስታውቀዋል፡፡

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት አዳሪ ትምህርትቤቶች በነበራቸው ጉብኝት ከአደረጃጀት ጀምሮ በተቋማቱ ያለው የመማር ማስተማር ስራ ከተመሰረተ ቅርብ ጊዜ የሆነው የአፋር ታለንት አካዳሚ በርካታ ልምድ ያገኘበት በመሆኑ ከ3.5 ሚሊዮን አመት በላይ እድሜ ያላትን እና ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኑዋን የምታረጋግጠውን የሉሲን ምስል ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ማበርከታቸውን አቶ መሀመድ ገልጸዋል፡፡ 

የአፋር የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ የአፋር ታለንት አካዳሚ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በመያዝ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ጉብኝት ማድረጉ በተማሪዎች መካከል ትውውቅ ከመፍጠሩ ባሻገር አዳሪ ትምህርትቤቶቹ የተቋቋሙበትን ተማሪዎችን በትምህርት ውጤታማ የማድረግ ተልዕኮ የሚያሳካ ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ስጦታውን በተረከቡበት ወቅት ጠቁመው የአፋር ትምህርት ቢሮ የክልሉም ሆነ የሀገራችን የቱሪስት መዳረሻ የሆነችውን የሉሲን ምስል በስጦታ መልክ በማበርከቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው በመግለጽ ቢሮው በቀጣይ ከአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የአፋር ታለንት አካዳሚ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙትን የእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ፤ የገላን የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ  እንዲሁም ብርሀን የአይነስውራን አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ተዘዋውረው በመመልከት ለሶስቱም አዳሪ ትምህርት ቤቶች በተመሳሳይ ስጦታ አበርክተዋል፡፡

.

Copyright © 2025 All rights reserved.