Home በከተማ አስተዳደሩ የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት በሚሰጥባቸው የመማሪያ ጣቢያዎች ድጋፍና ክትትል ተካሄደ።

በከተማ አስተዳደሩ የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት በሚሰጥባቸው የመማሪያ ጣቢያዎች ድጋፍና ክትትል ተካሄደ።

31st January, 2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክተር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት 6,461 ዜጎች በ324 የማስተማሪያ ጣቢያዎች የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርትን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ አስታወቀ።
የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት የከተማውንም ሆነ የሀገሪቱን የተማረ የሰው ሀይል ምጣኔ ከማሳደጉ ባሻገር ትምህርቱን የሚከታተሉ ዜጎች እንደፍላጎታቸው መደበኛ ትምህርት የሚማሩበትና በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የክህሎት ስልጠና ወስደው ህይወታቸውን የሚያሻሽሉበት መርሀግብር በመሆኑ ትምህርቱ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካል ኃላፊነቱን መወጣት እንደሚገባው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል ገልጸው ቢሮው ፕሮግራሙ በአግባቡ ተግባርራዊ በመደረግ ላይ መሆኑን በድጋፍና ክትትል የማረጋገጥ ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስገንዝበዋል።

የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት በመደበኛው ትምህርት የመማር እድል ላላገኙና እድሜያቸው ከ15 አመት በላይ ለሆነ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጥ ትምህርት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ ጠቁመው ትምህርቱ በዋናነት የዜጎችን የማንበብ የመጻፍና የማስላት ክህሎት በማዳበር ቀጣይ ህይወታቸው ውጤታማ እንዲሆን ታስቦ ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆኑን ትምህርቱ ከሚሰጥባቸው ጣቢያዎች መካከል ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኘው አብዲ ጃርሶ መማሪያ ጣቢያ ተገኝተው ድጋፍና ክትትል ባደረጉበት ወቅት አስታውቀዋል።

የቢሮው የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ባለሙያ አቶ አበበ ዘነበ በበኩላቸው በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት በከተማ አስተዳደሩ 6,461 ዜጎች በ324 የማስተማሪያ ጣቢያዎች በሳምንት ለስድስት ሰአት ትምህርቱን በመከታተል ላይ መሆናቸውን ገልጸው ትምህርቱ በ596 አመቻቾች እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

.

Copyright © All rights reserved.