Announcement የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ማህበረሰብ የአረንጋዴ አሻራ ተከላ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ማህበረሰብ የአረንጋዴ አሻራ ተከላ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

11th July, 2026

(ሀምሌ 1/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ማህበረሰብ የአረንጋዴ አሻራ ተከላ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር "ተስፋን እንትከል!" በሚል መሪ ሀሳብ ተካሄዳል፡፡

ለ8ኛ ዙር በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ፣ በትምህርት መዋቅሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የሚገኙ የትምህርት አመራሮች ፣ ባለሙያዎች ፣ መምህራንና ተማሪዎች በጥቅሉ ከ10 ሺ በላይ የሚሆኑ የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ "ተስፋን እንትከል!" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የ8ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ከቦሌ ወደ ጎሮ በሚወስደው አዲሱ የVIP መንገድ ላይ ተካሄዳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ከችግኝ ተከላ ባለፈ የአካባቢ ጥበቃን፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋምን እና ውብና አረንጓዴ ከተማ የመገንባት ራዕይን ለማሳካት ትልቅ ሚና ያለው ሀገራዊ ንቅናቄ መሆኑን ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም ኢትዮጵያ ለትላልቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ተመራጭ እንድትሆን ካደረጓት ዋነኛ ስኬቶች መካከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አንዱ መሆኑን ጠቅሰው የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ ከተከላው በኋላ የሚደረገው የእንክብካቤ ሥራ ከፍተኛ ዋጋ እንዳለው በመግለጽ የተተከሉትን ችግኞች በአግባቡ የመንከባከብ ኃላፊነትን በተከላው ላይ የተሳተፉ አካላት በሙሉ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ከ1.8 በላይ ችግኞችን ለመትከል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መከናወናቸዉን ገልጸው ለስኬቱ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.