Resource በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሞዴል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተካሄደባቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሞዴል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተካሄደባቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

01st March, 2025

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሞዴል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተካሄደባቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

(የካቲት 21/2017 ዓ.ም) በመስክ ምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ፣ የቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ወንድሙ ኡመር እንዲሁም የክፍለ ከተማው አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

ምልከታው ከተካሄደባቸው ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው ቦሬ ገላን  የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት አንዱ ሲሆን በትምህርት ቤቱ ግንባታው የተጠናቀቀ 20 የመማሪያ ክፍሎችን የያዘ ባለ አንድ ወለል ህንጻ ፣ የመመገቢያ አዳራሽና የአስተዳደር ቢሮዎችን ያካተተ ህንጻ የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም የትምህርት ቤቱን አጠቃላይ ምድረ ግቢው በመዘዋወር ምልከታ አድርገዋል።

መጋቢት 28 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሌላው ምልከታ የተደረገበት ተቋም ሲሆን ትምህርት ቤቱን ሞዴል ለማድረግ ምድረግቢውን ለህጻናቱ ምቹ የመማሪያ እና የመጫወቻ ስፍራ እንዲሆን ባለ ሁለት ወለል ህንጻ ለመገንባት የዲዛይን ስራ ተጠናቆ ግንባታውን ለመጀመር ዝግጅት መጠናቀቁ በምልከታው ተጠቁሟል።

.

Copyright © All rights reserved.