ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የሚገኘው የአብዲ ጃርሶ ት/ቤት ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ሌሎች የትምህርት ባለድርሻ አባላት የታላቁን ህዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ የድጋፍና የተሰማቸውን ደስታም ገልጸዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሌማንቾ የህዳሴው ግድብ የትምህርት ማህበረሰቡን ጨምሮ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ርብርብ አድርጎ ተገንብቶ የተመረቀ ኢትዮጵያም ሆነ ሌሎች የጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ነው ብለው በቀጣይም በህዳሴው ግድብ የታየው ሀገራዊ አንድነት፣ የጋራ መግባባትና ቁርጠኝነት በሌሎች ፕሮጀክቶች ላይ በመድገም የብልፅግና ጉዞአችንን ለማፋጠን የጋራ መነሳሳት የፈጠረ እንደሚገባ ገልፀዋል ።
.