የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በሳወቀው መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በሁሉም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ጤና ጣቢያዎች ላይ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
ክትባቱን ከየካቲት 9 እስከ 13/2018 ዓ.ም ድረስ ለተካታታይ 5 ቀናት ዕድሜያቸው 9 ዓመት የሆናቸው ታዳጊ ሴት ልጆች የሚከተቡ ሲሆን ከዚህ በፊት ያልተከተቡ ዕድሜያቸው ከ10 እስከ14 ዓመት የሆናቸው ታዳጊ ሴት ልጆችም ከትባቱን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡
የማህጸን በር ካንሰር ሂዮማን ፓፒሎማ /HPV/ በተሰኘ ቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን በወቅቱ ካልታከመ በሴቶች ላይ ከፍተኛ የህመም እና ሞት የሚያስከትል ሲሆን ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በገዳይነቱ በ2ኛ ደረጃ የሚገኝ የካንሰር ዓይነት እንደሆነም ጥናቶች ያመለክታሉ።
በሽታውን ለመከላከል ክትባት አንዱ እና ዋነኛው አማራጭ ነው፡፡
.