(ነሀሴ 29/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላዬ ዘውዴ ቢሮው ለአራት ተከታታይ አመታት ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ላመጣው ውጤት የሱፐርቪዥን አካል ትልቁን ሚና የተጫወተ መሆኑን ገልፀው ይህን የስራ ድል በጀመርነው በጀት ዓመት በተሻለ መንገድ ለመድገም በክፍለ ከተማና በተዋረድ ያሉ የሱፐር ቪዥን አካላት ድጋፍ የራሱ ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን አብራርተው፡፡
ሱፐርቫይዘሮች ተቆጥሮ የተሰጣቸዉን ሥራ በውጤት ለማጠናቀቅ መምህሩ ካሪኩለሙና ተማሪው መገናኘታቸውን በማረጋገጥ የመማር ማስተማር ስራውን ስኬታማ የማድረግ እንዲሁም የመጨረሻ ግብ የሆነውን የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ላይ ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል:: የሚደረጉ የሱፐርቪዥን ስራዎችን በጥራት በመስራት ትክክለኛ መረጃ በማምጣት ፤ በመደገፍ ለሚመለከተው አካል የመረጃ ምንጭ በመሆን መስራት ይገባል ብለዋል::
የዳይሬክቶሬቱ ሱፐር ቪዥን ቡድን መሪ ወ/ሮ ባንቺዓለም ጌታቸው የ2019 የትምህርት ዘመን የቅድመ ዝግጅት ሥራን አስመልክቶ በክፍለ ከተማ ደረጃ በተዘጋጀ ቼክ ሊስት መሰረት የድጋፍና ክትትል ሥራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው ትምህርት ቤቶች በቅድመ ዝግጅት ሥራ ማለትም በግብዓት ፣ በመምህር መሟላት ፣ እቅድ ዝግጅትና ለመጀመሪያ ቀን የትምህርት አጀማመር (Day one Class one) ዝግጁ መሆናቸዉ ማረጋገጥ ከሱፐርቪዥን መዋቅሩ መረጋጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
.