Announcement በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት በሬዲዮ ስርጭት ነገ ይጀምራል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት በሬዲዮ ስርጭት ነገ ይጀምራል፡፡

22nd September, 2025

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት በሬዲዮ ከነገ እለት ማለትም ከ12/1/2018 ዓ.ም ጀምሮ መሰራጨት የሚጀምር መሆኑ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ዲናኦል ጫላ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን ትምህርት በሬዲዮ ከነገ እለት ጀምሮ መሰራጨት የሚጀምር መሆኑ የገለጹ ሲሆን የሬዲዮ ትምህርቱ ለመደበኛ ትምህርቱ አጋዥ እና ተማሪዎች በቀላሉ መረዳት እንዲችሉ አቅም የሚሆን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አያይዘዉም የትምህርት ስርጭቱን በመጣው የሬዲዮ ትምህርት ስርጭት መርሀ ግብር መሰረት ተማሪዎች በአግባቡ እንዲከታተሉት ማድረግ ላይ መምህራን ፣ የትምህርት ባለሙያዎች ፣ ሱፕርቫይዘሮችና የትምህርት አመራሮች ትልቅ ሀላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሀላፊው አክለዉም በመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት ላይ 15 እና በሁለተኛው ወሰነ ትምህርት ላይ 15 በጥቅሉ 30 ትምህርቶች የሚሰራጩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
.

Copyright © All rights reserved.