በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በሚገኙ በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት የትምህርት ዘመን ትምህርት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል፡፡
በክፍለ ከተማዉ አቡነ ባስሊዮስ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሔደዉ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የክፍለ ከተማዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አሊ ከማል ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የምገባ ኤጀንሲ የፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አስጨንቅ ብርሀኑ ፣የክፍለ ከተማዉ ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ዘዉዴን ጨምሮ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች እና መምህራን የተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል፡፡
በትምህርት ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል ለትምህርት ዘመን መክፈቻ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት በማስተላለፍ ትምህርት ቤቶች የነገ ሀገር ተረካቢዎች የሚፈሩበት ተቋም መሆኑን ገልፀው ተማሪዎች ፣መምህራን እንዲሁም የወላጆች ድጋፍን በማጠናከር የተማሪ ውጤት እንዲሻሻል በተሻለ ትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
ወላጆች ልጆቻቸውን በስነ ምግባር የታነፁ የማድረግ ስራ እንዲሰሩም ጥሪቸውን አስተላለፈዋል፡፡
አቶ ቴዎድሮስ አክለው የክፍለ ከተማው አስተዳደር ለትምህት ዘርፍ እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንደሚያጠናክርም ተናግረዋል።
.