Home የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች እና የመምህራን የስፖርት ሊግ ውድድርን በድምቀት አጠናቀቀ።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች እና የመምህራን የስፖርት ሊግ ውድድርን በድምቀት አጠናቀቀ።

31st January, 2026

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ በመዝጊያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት ቤቶች የበርካታ ስፖርታዊ ተሰጥኦዎች መፍለቂያ መሆናቸውን ገልጸዋል። 

ስፖርታዊ ውድድሮች በወጣቶች መካከል ያለውን ወንድማማችነት ከማጠናከራቸው ባለፈ ለሀገር ሰላምና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ተማሪዎች በትምህርታቸው ጎን ለጎን በስፖርቱ ዘርፍ ውጤታማ በመሆን ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ  በበኩላቸው ስፖርታዊ ውድድሮች ተማሪዎች በአካል ብቃት ዳብረው በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑና ማህበራዊ ትስስራቸው እንዲጎለብት እንደሚያስችል ገልጸዋል። 

የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰማሀኝ አስታጥቄ በበኩላቸው ውድድሩ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተገነባ ትውልድ ከመፍጠር ባለፈ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው፤ አሸናፊዎች በቀጣይ በከተማ ደረጃ በሚካሄደው ውድድር ክፍለ ከተማውን ወክለው እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል።

በመዝጊያ ጨዋታዎቹ በመምህራን መካከል በተደረገ ግጥሚያ ጠመንጃ ያዥ ትምህርት ቤት ምስራቅ ጎህን 4 ለ 3 በማሸነፍ አሸናፊ ሲሆን፤ በተማሪዎች የእግር ኳስ ፍጻሜ ደግሞ ዳንዲ ቦሩ ትምህርት ቤት ሽመልስ ሀብቴን 1 ለ 0 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

.

Copyright © All rights reserved.