Resource ቢሮው በ2017 ዓ.ም 6 ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት መሰረት ያደረገ ኢንስፔክሽን ተካሄደ።

ቢሮው በ2017 ዓ.ም 6 ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት መሰረት ያደረገ ኢንስፔክሽን ተካሄደ።

15th February, 2025

ቢሮው በ2017 ዓ.ም 6 ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት መሰረት ያደረገ ኢንስፔክሽን ተካሄደ።

(የካቲት 7/2017 ዓ.ም) ኢንስፔክሽኑ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን እና ልማት ቢሮ በመጡ ባለሙያዎች የተካሄደ ሲሆን ከኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ለቀረቡ የተለያዩ ጥያቄዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና በአቶ ሳምሶን መለሰ ፣ በቢሮ ሀላፊ አማካሪ በወ/ሮ አበበች ነጋሽ እና በቢሮው ዳይሬክቶሬቶች ምላሽና ማብራሪያ ተሰቷል።

ኢንስፔክሽኑ ቢሮው በበጀት አመቱ በ6 ወራት ውስጥ ከተማሪ ቅበላ ጀምሮ በቁልፍ አመላካች የተቀመጡ ተግባራት አፈጻጸምን በማየት በቀሪ የትግበራ ምዕራፎች የተሻለ ስራ መስራት እንዲቻል ታስቦ እንደሚካሄድ በፕላን እና ልማት ቢሮ የተቋማት ስራ አፈጻጸም ቡድን መሪ ወይዘሮ አለምወርቅ ያሲን ገልጸው ኢንስፔክሽኑ ከቢሮ ባሻገር በተመረጡ ትምህርትቤቶችም የሚካሄድ መሆኑን አስታውቀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን እና ልማት ቢሮ አማካይነት ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በ6 ወራት ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት አድርጎ የሚደረገው ኢንስፔክሽን የመማር ማስተማር ስራው ምንያህል ውጤታማ እየሆነ እንደሚገኝ በማየት በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንዲቻል አቅጣጫ የሚቀመጥበት አሰራር እንደመሆኑ ቢሮው በቀጣይ በኢንስፔክሽን የሚሰጡ ግብረመልሶችን መሰረት በማድረግ በላቀ ትጋት እንደሚሰራ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ አመላክተዋል።


.

Copyright © All rights reserved.