የተማሪ ወላጅ ማህበር (ተ.ወ.ማ) የ2017 ዓ.ም የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀምን ገመገመ::
(የካትት 28/2017 ዓ.ም) የተማሪ ወላጅ ማህበሩ በ 2017 ዓ.ም የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ላይ እንዲሁም በትምህርት ቤቶች ያሉ የመማር ማስተማር ሥራዎች ፣ ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ሥራ ምቹ ከማድረግ አንፃር እንዲሁም የተማሪ ምገባን አስመልክቶ በናሙናነት በተመረጡ ትምህርት ቤቶች በተደረገ ድጋፍና ክትትል ሪፖርት ላይ ውይይት አድርጓል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር በውይይቱ ላይ ተገኝተው በውይይቱ የተነሱ ጥያቄዎች የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ብቁ ዜጋ የማፍራት ሂደቱን ለማገዝ ቀጣይ ትልቅ ሥራ ለመስራት ዝግጅት እንድታደርጉ መነሳሳት ይፈጥራል ብለዋል :: ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም በቀጣይ 6 ወራት የተማሪ ወላጅ ማህበሩ በትምህርት ለትውልድ ሥራ በተማሪ ውጤትና ስነምግባር ላይ አመርቂ ውጤት ለማምጣት ከትምህርት ማህበረሰቡና ከወላጆች ጋር ልዩ ትኩረት በመስጠት እንዲሰሩ አሳስበዋል ::
የተማሪ ወላጅ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሐሰን ሺፋ በበኩላቸው ውይይቱን በመሩበት ወቅት እንዳሉት የቀረበው ሪፖርት ማህበሩ በ6 ወራት ያከናወናቸው ሥራዎች እንዲሁም በድጋፍና ክትትል ስራው የታዩ ውጤቶች የተማሪ ወላጅ ማህበሩ የትምህርት ስራው በጥራት እንዲከናወን ሰፊ ሥራ እየሰራ መሆኑን እንደሚያሳይ ገልፀዋል:: አክለውም በቀጣይም የተማሪ ወላጅ ማህበሩ አባላት ሥራዎችን በእቅዳቸው መሰረት ለመስራት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ያደርጋል ብለዋል::
አቶ ቀፀላ ፍቅረማርያም የተማሪ ወላጅ ማህበሩ በመማር ማስተማር ስራው ላይ በጎ ተፅእኖ በማሳደርና ለትምህርት ስራው አጋዥ በመሆን የተማሪ ውጤትን ለማሳደግ ፣ የትምህርት ተቋምን ምቹ ለማድረግና በተማሪ ባህሪ ማሻሻል ላይ ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ሪፖርቱ እንደሚጠቁም ተናግረዋል ::
በቀጣይም በክፍለ ከተሞች የተሰሩ መሰል የስራ አፈፃፀም ሪፖርቶች ቀርበው አንዱ ከሌላው የሚማርበት ዕድል እንዲፈጠር በማለት ጠይቀዋል::
በውይይቱ የሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ተማሪ ወላጅ ማሕበር አባላት ተሳትፎ አድርገዋል ::
.