About የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2017ዓ.ም የተማሪዎችና መምህራን የሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይ በዳግማዊ ሚኒሊክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ አካሄደ።

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2017ዓ.ም የተማሪዎችና መምህራን የሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይ በዳግማዊ ሚኒሊክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ አካሄደ።

12th April, 2025

(ሚያዝያ 3/2017ዓ.ም) አውደ ርዕዩ "የፈጠራ ስራን ከቃል ወደ ባህል" በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ ተማሪዎችና መምህራን የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ቀርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት  በትምህርት ዘርፉ የሚሰሩ የሳይንስ የፈጠራ ስራዎች የተማሪዎችን እምቅ አቅም በማሳየት በከተማም ሆነ በሀገር አቀፍ  ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን  እንዲችሉ የሚያስችል ተግባር መሆኑን ጠቁመው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በተማሪዎችና መምህራን እየተሰሩ የሚገኙ የፈጠራ ስራዎች ለሚፈለገው አላማ መዋል እንዲችሉ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል።

የአራዳ ክፍለ ከተማ  ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማዕረግ ግርማይ ያደጉ ሀገራት አሁን የደረሱበት ደረጃ መድረስ የቻሉት በየትምህርት ቤቱ የሚገኙ ታዳጊ ተማሪዎች ላይ በአግባቡ መስራት በመቻላቸው መሆኑን ጠቁመው በዛሬው አውደ ርዕይ የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች ተማሪዎቻችን ምን ይህል የፈጠራ ብቃት እንዳላቸው የተረጋገጠበት መሆኑን አስታውቀዋል።

በተማሪዎች እና መምህራን የሚቀርቡ የሳይንስ የፈጠራ ስራዎች በክፍል ውስጥ በንድፈ ሀሳብ የሚሰጠውን ትምህርት  በተግባር የሚታይበት ከመሆኑ ባሻገር የፈጠራ ስራዎቹ ለህብረተሰቡ ቀርበው ለፈጠራ ባለቤቶቹ አድናቆት የሚቸርበት መሆኑን  የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ደበሌ ገልጸው  በክፍለ ከተማ ደረጃ በተዘጋጀው አውደ ርዕይ የተሻለ የፈጠራ ስራ አቅርበው አሸናፊ የሚሆኑት በከተማ ደረጃ በሚካሄድ ተመሳሳይ መርሀ ግብር ተሳታፊ እንደሚሆኑ አስረድተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.