የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በውጤታማነት ለመስጠት ተማሪዎችን ኦላይን ፈተና ወደሚሰጥባቸው የመፈተኛ ጣቢያዎች በሰዓቱ እንዲደርሱና ፈተናዉን ሳጠናቅቁ እንዲመለሱ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎችና የክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊዎች በተገኙበት አካሄዳል፡፡
በውይይቱ ላይ በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወን በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ መዋቅሩ አመራሮችና አባላት እያደረጉ ለሚገኘው የማይቋርጥ ድጋፍ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ምስጋና አቅርበው ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከተማ ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በኦላይን የሚሰጥ በመሆኑ ፈተና መስጫ ጣቢያዎች ላይ ተማሪዎች በሰዓቱ እንዲደርሱና ፈተናቸዉን ሳጠናቅቁ እንዲመለሱ ለማድረግ ተሸከርካሪ አቅራቢዎች የተገኙ መሆኑን ጠቅሰው በስራዉ ሂደት ላይ በመወያየት ከመግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡