Resource የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ኦን ላይን ለመስጠት በተዘጋጀ ማስፈጸሚያ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ኦን ላይን ለመስጠት በተዘጋጀ ማስፈጸሚያ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

22nd February, 2025

የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ኦን ላይን ለመስጠት በተዘጋጀ ማስፈጸሚያ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

(የካቲት 13/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ ኦን ላይን ለመስጠት በሚያስችል እቅድ ላይ ከክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አካሂዳል፡፡

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ዳኜ የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ የተዘጋጀን እቅድ አቅርበው ውይይት ተካሄዳል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፈቃዱ መድረኩ ቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለሚደረግ ውይይት ሰፊ ግብአት የሚገኝበት መሆኑን ጠቁመው በ2016 ዓ.ም ፈተና አሰጣጥ የነበሩ ችግሮችን በመለየት ከችግሩ መውጫ ለማመቻቸት ቀደም ብሎ በእቅድ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ አያይዘውም በየትምህርት ቤቱ ያሉ የአይቲ ባለሙያዎችንና ግብአቶችን በአግባቡ መጠቀም ለፈተናው ስኬት የራሱ ሚና እንዳለው በመረዳት መስራት እንደሚያስፈልግ  አሳስበዋል::

.

Copyright © All rights reserved.