Resource ከቅድመ አንደኛ ትምህርት አተገባበር ጋር በተገናኘ በገላን ቁጥር 2 ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልምድ ልውውጥ ተካሄደ።

ከቅድመ አንደኛ ትምህርት አተገባበር ጋር በተገናኘ በገላን ቁጥር 2 ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልምድ ልውውጥ ተካሄደ።

21st December, 2024

ከቅድመ አንደኛ ትምህርት አተገባበር ጋር በተገናኘ በገላን ቁጥር 2 ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልምድ ልውውጥ ተካሄደ።

(ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም) በልምድ ልውውጡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት  ዕሳነ መምህራንን ጨምሮ የቅድመ አንደኛ አስተባባሪዎች፣ የክፍለ ከተማ ዘርፈ ብዙ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን የልምድ ልውውጡ ተሳታፊዎች የትምህርት ቤቱን ምድረ ግቢ፣የመጫወቻ ቦታዎች ፣ የመማሪያ ክፍሎችና የመመገቢያ ቦታውን በመዘዋወር ምልከታ አካሂደዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ቡድን መሪ ወይዘሮ ፍሬሕይወት በቀለ  ቢሮው  በ118 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባደረገው ድጋፍና ክትትል ገላን ቁጥር 2 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት  የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው ተቋማት መካከል አንዱ  በመሆኑ ልምድ ልውውጡን ማካሄድ ማስፈለጉን ጠቁመው የልምድ ልውውጡ ተ ሳታፊዎችም ትምህርት ቤቱ ጫወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነ ዘዴ ተግባራዊ ያደረገበትንም ሆነ ትምህርት ቤቱ ለህጻናቱ ምቹ እንዲሆን የተከናወኑ ተግባራትን በማየት በየትምህርት ቤቶቻቸው ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው አዝገንዝበዋል።

በትምህርት ቤቱ የሚገኙ  የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ለትምህርት ደረጃው በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል እንዲችሉ የወላጅ ኮሚቴዎችን ጨምሮ በአከባቢው የሚገኙ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን በማ ስተባበር ባከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆን መቻሉን የገላን ቁጥር 2 ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር አቶ ኦሊያድ ዋንጋሪ ገልጸው ለተቋሙ ውጤታማነት መምህራንን ጨምሮ አጠቃላይ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰቦችም ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ገላን ቁጥር 2 ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመማሪያ ክፍሉ ካዘጋጀው የኮርነር አደረጃጀት ጀምሮ በራሱ የውስጥ አቅም የተማሪዎችን ዕድሜ ያማከለ የመመገቢያ አዳራሽ ከማዘጋጀት ጀምሮ የውሀ ቧንቧዎችና አጠቃላይ ምድረ ግቢው ለሌሎች ተሞክሮ መሆን ስለሚችል ልምድ ልውውጡን ማካሄድ ማስፈለጉን የቢሮው የቀዳማይ ልጅነት ባለሙያ አቶ ስንታየሁ መኮንን ገልጸዋል።

, , .

Subscribe to receive inspiration, ideas, and news in your inbox.

Copyright © All rights reserved.