የቢሮ ጠቅላላ ካውንስል አባላት የቢሮውን የስርዓተ ትምህርት ዝግጀትና ትግበራ እና የግዥ ዳይሬክቶሬትን የ15 ቀናት እቅድ አፋጻጸም ገመገሙ።
(የካቲት 14/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጠቅላላ ካውንስል አባላት የቢሮውን የስርዓተ ትምህርት ዝግጀትና ትግበራ እና የግዥ ዳይሬክቶሬትን የ15 ቀናት እቅድ አፈፃፀምን ከመደበኛ እቅድ አፈጻጸምና ከሪፎርም ስራዎች አተገባባር አካያ ግምገማዉን አካሂዳል።
በግምገማው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ግምገማው ተጠናክሮ መቀጠሉ የተሻለ የስራ አፈጻጸም እንዲኖር የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰው ጠቅላላ ካውንስሉ በየጊዜው የሚከናወኑ ስራዎችን አፈጻጸምና የሚደረጉ ድጋፍና ክትትሎችን በየጊዜው እያየና እየገመገመ መሄድ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
የቢሮ ሀላፊ አማካሪና የዘርፉ ሀላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ጠቅላላ ካውንስሉ በየ15 ቀኑ ውይይቶችንና ግምገማዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ በመግለጽ በዛሬው መድረክ የቢሮው የስርዓተ ትምህርት ዝግጀትና ትግበራ እና የግዥ ዳይሬክቶሬትን የ15 ቀናት እቅድ አፋጻጸም ከመደበኛ እቅድ አፈጻጸምና ከሪፎርም ስራዎች አተገባባር አካያ ለግምገማ መቅረቡን በመጥቀስ በቀጣይ ሁሉም ዳይሬክቶሬቶች በወጣው መርሀ ግብር መሰረት እቅድ አፈጻጸማቸዉን የሚያቀርቡና የሚገመገም መሆኑን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው የሚቀርቡ ሪፖርቶች ለሌሎች የመማማሪያ መድረክ እንዲሆን የሚያግዝ እንዲሁም ምን ያህል ተግባራትን እያከናወንን እንደምንገኝ የምናይበትና የተቀራረበ አፈጻጸም እንዲኖር የሚረዳ በመሆኑ ውይይቱ ትኩረት ተሰጥቶት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
.