About የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያ በሚሰጠው የፈተና ገለጻ/Orientation/ ላይ መገኘት እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡

የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያ በሚሰጠው የፈተና ገለጻ/Orientation/ ላይ መገኘት እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡

28th June, 2025

 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት በቂ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በከተማ አስተዳደሩ የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉን እንዲሁም ፈተናው ከሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ የገለጹ ሲሆን ተማሪዎች በፈተና መስጫ ጣቢያዎች በወጣው መርሀ ግብር መሰረት በመገኘት ፈተናዉን ሊወስዱ ይገባል ብለዋል፡፡ 

አቶ ዲናኦል አክለዉም የፈተና አሰጣጡን አስመልክቶ ገለጻ በፈተና ጣቢያዎች የሚሰጥ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ የሁለተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት የሚሰጠውን የፈተና ገለጻ/Orientation/ መከታተልና የመፈተኛ ቦታቸዉንና ክፍላቸዉን ማየት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
.

Copyright © All rights reserved.