Home አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በሚገኘው አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 4 በ 1 ሁለገብ ሜዳ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በሚገኘው አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 4 በ 1 ሁለገብ ሜዳ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

28th February, 2026

ሁለገብ ሜዳው የሜዳ ቴኒስ ፣የመረብ ኳስ፣የእጅ ኳስ እና የቅርጫት ኳስ መጫወቻዎችን ያካተተ ሲሆን የሜዳ ግንባታው ከካናዳ ሀኪሞች ልማት ድርጅት በተገኘ 5 ሚሊየን ብር ተገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጉን በምረቃ መርሀግብሩ ተገልጿል። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የካናዳ ሀኪሞች ልማት ድርጅት በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዚህ መልኩ ደረጃውን የጠበቀ ሁለገብ ሜዳ  አስገንብቶ ለአግልግሎት በማብቃቱ ለድርጅቱ አመራሮችና ገንዘቡን ለለገሱ አካላት ምስጋና አቅርበው የሜዳው መገንባት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት በተግባር ተለማምደው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን በመግለጽ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤቱን ምድረ ግቢ ምቹ የማድረግን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጄና በበኩላቸው በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤት ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ምቹ የስፖርት ማዘውተሪያ ሁለ ገብ ሜዳ ተማሪዎች የተሟላ ስብዕና ተላብሰው በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ከማስቻሉ ባሻገር ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው የክፍለ ከተማው አስተዳደር ለትምህርት ሴክተሩ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል።

የካናዳ ሀኪሞች ልማት ድርጅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመስራት ለአገልግሎት በማብቃት ላይ መሆኑን የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ ሚስ ካትሪን ሎፌር ገልጸው በአዲስ አበባ ከተማ በ11 ትምህርት ቤቶች ምድረ ግቢ አረንጓዴ ከማድረግ ባሻገር ደረጃውን የጠበቀ ሁለገብ ሜዳ በመገንባት ለአገልግሎት የማብቃት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ በመጥቀስ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ሁለገብ ሜዳውን በአግባቡ በመጠቀም ተማሪዎችን ውጤታማ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።


.

Copyright © All rights reserved.