Resource በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመምህራንና የተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር የማጠቃለያ መርሀ ግብር ተካሔደ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመምህራንና የተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር የማጠቃለያ መርሀ ግብር ተካሔደ።

08th March, 2025

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመምህራንና የተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር የማጠቃለያ መርሀ ግብር ተካሔደ። 

(የካቲት 28/2017 ዓ.ም)  በክፍለ ከተማው ትምህርት ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት  ‹የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ሊግ ባህል በማድረግ ጤናማ ፣ ንቁና ፣ ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን›  በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ የቆየው ውድድር በክፍለ ከተማው ወረዳ 07 አስተዳደር ሮም ሜዳ የማጠቃለያና የእውቅና መርሀ ግብር ተከሔዷል።

በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ የተገኙት የክፍለ ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ ስፖርታዊ ውድድሩ ተተኪዎችን ከማፍራት በተጨማሪ ወንድማማችነት ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀው በየደረጃው የውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ተናግረዋል ።

የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ በበኩላቸው በውድድሩ በሁለቱም ፆታዎች በበርካታ የስፖርት ዘርፎች በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት ሲካሄድ መቆየቱን ገልፀዋል።

 አቶ ገነነ አክለውም ስፖርታዊ ውድድሩ በትምህርት ተቋማት ከቀለም ትምህርት ጎን ለጎን ተማሪዎችና መምህራን በአካል ብቁ እንዲሆኑ፤ የባህል መወራረስና መተባበር እንዲዳብር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

ስፖርታዊ ውድድሩ በእግር ኳስ፤መረብ ኳስ፤አትሌቲክስ፤ጠረጴዛ ቴኒስ፤እጅ ኳስ፤ቅርጫት ኳስ፤ውሀ ዋናና ገመድ ጉተታ የስፖርት አይነቶች ሲካሄድ የቆየ ሲሆን የውድድሩ አሸናፊዎች እና ውድድሩ የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበራቸው ተቋማት እውቅናና ሽልማት መሰጠቱን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

.

Copyright © All rights reserved.